=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ልቡ ጥሩ አሳቢ ምላሱ የገራ፤
ብዙ የሚሠማ ትንሽ የሚያወራ፤
ፊቱ በተዋዱዕ በኢማን ያበራ፤
ፈገግታው የሚስብ ከሩቅ የሚጣራ፤
በፈርዱ የቆመ ከሱናውም ያለ፤
ደበረኝ ሰለቸኝ ደከመኝ ያላለ፤
ለረጅሙ ጉዞ ጥሩን የሰነቀ፤
ለማይቀረው ዓለም መሄዱን ያወቀ፤
ፀባዩ የሚጥም ወግ አመሉ ሸጋ፤
እኔስ ሰው ጠፍቶኛል እንሂድ ፍለጋ፤
ልቤን ሰው ሰው አለው የኢማን ጋደኛ፤
ቀኑን ፁሞ የሚውል ሌሊቱን የማይተኛ፤
በአሁኑ ሰዓት ስለኢስላም የሚያስታውሰ ፣ ስለቀብር ፣ ስለቂያማ ቀን ፈተና አስታዋሽ ጏደኛ ማግኘት ከባድ እየሆነ መቷል። እያንዳንዱ ሰው ጥቅሙን እንጂ ሌላን አያስብም። ዛሬ ጏደኛ ብለን የያዝነው ሰው ጥቅሙ ሲቀርበት ይርቀናል።
መልካም ጏደኛ ከመፈለጋችን በፊት እራሳችን መልካም ጏደኛ ለማድረግ እንስራ!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|